ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ESSTI) ጋር በመተባበር “በጠፈር ላይ የተመሰረቱ ቴክኖሎጂዎች እና መተግበሪያዎችለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ ጉባኤ በነገው ዕለት ያካሂዳል፡፡
የጉባኤው ዋንኛ ዓላማ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገውን ስምምነት ዓላማ ፣ የትብብር ወሰን እና አጠቃላይ ማዕቀፍ ለዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች እና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማስተዋወቅ፤ በሁለት ወገኖች መካከል የተፈረመውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ቁልፍ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ቦታዎችን ለይቶ ማወቅ እንዲሁም ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ የአካዳሚክ እና የምርምር ሰራተኞች አባላት በጋራ መግባባት ላይ በተካተቱት ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፉ ማነሳሳት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዚህ ኮንፍራንስ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
በነገው ዕለት ማለትም ቀን በ06/01/2014 ዓ.ም በተማሪዎች መመረቂያ አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን፤ የዩኒቨርሲቲው ሴኔት አባላትና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ከጠዋቱ 2፡30 በመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ያሳስባል፡፡