የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ – መንግስት” ንቅናቄ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው ዕለት ተጀመረ። (መስከረም 8/2014 ዓም፣ወሶዩ)
“የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል።
በዘመቻው ከ 21 ሺህ የሚበልጡ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እና በክረምት የትምህርት መርሃ ግብር እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
*************
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰን ጨምሮ፣ የዩኒቨርሲቲው አማካሪ ምክር ቤት አባላት፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች እና የንግዱ ማህበረሰ አባላትበተገኙበት ደብዳቤ የመላክ መርሃ ግብሩ በይፋ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት የደረሰውን ቀውስ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ ይህ የነጭ ደብዳቤ ማዕብል ትክክለኛ የሆነውን እውነታ ያስረዳል ሲሉ ተናግረዋል።
የሽብርተኛው ቡድን የፈፀመውን ጭፍጨፋ እና በንፁሃን ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ለቀረው አለም ለማስረዳት አዋጭ የዲፕሎማስ መንገድ መከተል ይገባል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን እውነታ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ የተጀመረው “ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት” ዘመቻን ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በሙሉ ሊቀላቀል ይገባል ሲሉ ፕ/ር ታከለ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሚላከው የነጭ ፖስታ የዲፕሎማሲ ተሳትፎ በዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሥራ መስኮች በቋሚና በጊያዊነት የተቀጠሩ 10 ሺህ ሰራተኞችን ጨምሮ በክረምት የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ከ11 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።